ሞሮኮና የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ!

በዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ሩብ ፍጻሜ የገባችው ሞሮኮ በውድድሩ ላይ ያላትን ታሪክ ምን ይምስላል?

  • ሞሮኮ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ ለስድስተኛ ጊዜ ነው።
  • የአትላስ አንበሶች ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ የተሳተፉት እ.አ.አ በ1970 በሜክሲኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው ዘጠነኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ነበር።
  • በምድብ አራት የነበረችው ሞሮኮ በጀርመን(በወቅቱ ምዕራብ ጀርመን) 2 ለ 1 እንዲሁም  በፔሩ 3 ለ 0  ስትሸነፍ በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ነጥቧን ከቡልጋሪያ ጋር አንድ አቻ በመውጣት አግኝታለች።
  • ሁማኔ ጃሪር ሞሮኮ በጀርመን 2 ለ 1 ስትሸነፍ ያስቆጠራት ግብ ለአትላንስ አንበሶች በዓለም ዋንጫው የተመዘገበት የመጀመሪያ ጎል ሆናለች።
  • ሰሜን ሜቄዶኒያዊው (በቀድሞ አጠራሯ ሜቄዶኒያ) ብላጎጂ ቪዲኒች ሞሮኮን በመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ በአሰልጣኝነት መርተዋል።
  • ሞሮኮ እ.አ.አ. 1986 ሜክሲኮ ባሰናዳችው 13ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ተሳትፎዋን ማድረግ ችላለች።
  • የአትላንስ አንበሶች በነበሩበት ምድብ ስድስት ፖርቹጋልን 3 ለ 1 በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ድላቸውን አስመዘገቡ።
  • አብደራዛቅ ካይሪ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አብዱልከሪም መሪ ቀሪዋን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
  • ከፖላንድና እንግሊዝ ያለ ምንም ግብ አቻ በመውጣት በአጠቃላይ በአምስት ነጥብ ምድቧን በመሪነት በማጠናቀቅ ወደ ጥሎ ማለፉ ገባች።
  • በጥሎ ማለፉ በሎተር ማቲያስ ጎል በጀርመን(በወቅቱ ምዕራብ ጀርመን) 1 ለ 0 ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።
  • በ1994 በአሜሪካ አስተናጅነት በተካሄደው 15ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በምድብ ስድስት የነበረችው ሞሮኮ በኔዘርላንድስ፣ሳዑዲ አረቢያ እና ቤልጂየም ተሸንፋ ከምድቧ ወድቃለች።
  • ሞሮኮ እ.አ.አ በ1998 በፈረንሳይ አስተጋጅነት በተካሄደው 16ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ በምድብ አንድ በነበራት ተሳትፎ ስኮትላንድን 3 ለ 0 አሸንፋ በብራዚል 3 ለ 0 ተረታ ከኖርዌይ ሁለት አቻ በመውጣት በአራት ነጥብ ከምድቧ ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።
  • የአትላስ አንበሶች አምስተኛ የዓለም ዋንጫ የተሳተፉት ከአራት በፊት በሩሲያ አስተናጋጅነት የተካሄደው 21ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ነው።
  • ሞሮኮ በነበረችበት ምድብ ሁለት በፖርቹጋል እና ኢራን በተመሳሳይ 1 ለ 0 ተሸንፋ ከስፔን ሁለት አቻ ተለያይታ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛ ከምድቧ ወድቃለች።
  • ሞሮኮ በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ሁለት የማጣሪያ ዙሮችን ማለፍ ነበረባት።
  • በዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ በምድብ ዘጠኝ የነበረችው ሞሮኮ ጊኒ፣ጊኒ ቢሳውን እና ሱዳን በተመሳሳይ ሁለት ሁለት ጊዜ አሸንፋ በ18 ነጥብ ወደ መጨረሻ ዙር ማጣሪያ አለፈች።
  • በመጨረሻው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ የአትላንስ አንበሶች ዴሞክራቲክ ሪፕሊክ ኮንጎን በደርሶ መልስ ውጤት 5 ለ 2 በማሸነፍ ለ22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ አለፈች።
  • በኳታር አስተጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የዘንድሮ ዓለም ዋንጫ ሞሮኮ በነበረችበት ምድብ ስድስት የእግር ኳስ ኃያሏን ቤልጂየም 2 ለ 0 በማሸነፍ በውድድሩ ያልተጠበቀ የተባለውን ውጤት አስመዘገበች።
  • የአትላስ አንበሶች ካናዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ከክሮሺያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታ በሰባት ነጥብ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ ለሁለተኛ ጊዜ መድቧን በመሪነት በማጠናቀቅ ወደ ጥሎ ማለፉ ገባች።
  • ሞሮኮ ትናንት በኢጁኬሽን ሲቲ ስታዲየም ከስፔን ጋር ባደረገችው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በመለያ ምት 3 ለ 0 በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫው ለሩብ ፍጻሜ ቻለች።
  • የአትላንስ አንበሶች ካሜሮን፣ሴኔጋል እና ጋና ተከትላ ሩብ ፍጻሜ የገባች አራተኛ አፍሪካዊት አገር ሆናለች።
  • ሞሮኮ የሩብ ፍጻሜውን ጨዋታዋን የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከፖርቹጋል ጋር በአል ቱማማ ስታዲየም ከምሽቱ 12 ሰአት ታደርጋለች።
  • ሞሮኮ የዘንድሮውን ጨምሮ በስድስት የዓለም ዋንጫዎች ባደረገቻቸው 20 ጨዋታዎች አምስት ጊዜ ስታሸንፍ ዘጠኝ ጊዜ ተሸንፋ ስድስት ጊዜ አቻ ወጥታለች።
  • የአትላንስ አንበሶች በዓለም ዋንጫው 15 ግቦችን ሲያስቆጥሩ 26 ግቦች ተቀጥሮባቸዋል።
  • የ47 ዓመቱ ዋሊድ ሬግራጉዊ ሞሮኮን ለዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ያሳለፉ የመጀመሪያ አሰልጣኝ ሆነዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም