ቀጥታ፡

የቶግ ውጫሌ ከተማ ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ እንሰራለን--የከተማዋ አስተዳደር

ጅግጂጋ ኢዜአ ህዳር 27 ቀን 2015 በሶማሌ ክልል የቶግ ውጫሌ ከተማን ለኑሮ ምቹ ለማድረግና ጊዜው ሚጠይቀውን አገልግሎት ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ።

በከተማዋ በግንባታ ላይ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ አባል ከንቲባዎች ተጎብኝተዋል።

May be an image of 9 people, people standing and indoor

ጎብኚዎቹ በኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ አዘጋጅነት በጅግጅጋ ከተማ የተጀመረው የተሞክሮና የመማሪያ መድረክ ተሳታፊ ከተሞች አመራሮች ናቸው።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ሙህየዲን አብዲ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የጠረፍ ከተማ በሆነችው ቶግ ውጫሌ በአሁኑ ወቅት በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደባት ነው።

በአነስተኛ ወጪ የሚገነቡ መኖሪያ ቤቶች፣ የእንግዳ ማሪፊያ፣ የከንቲባ ቢሮና የገበያ ማዕከል እንዲሁም የስደተኞች ማቆያ ማዕከል ከፕሮጀክቶቹ መካከል እንደሚገኙበት በአብነት አንስተዋል።

ከተማዋን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የተለያዩ ግንባታዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ገልጸዋል።

May be an image of 9 people, people standing and road

ከተሜነትን በማስፋፋት የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት መድረኩ ጠቃሚ አሰተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ያሉት የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አንዱዓለም ጤናው፤ የከተሞች አመራሮች እርስ በርስ እንዲማማሩና አቅማቸውን እንዲገነቡ ለማስቻል የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የቶግ ውጫሌ ከተማ ውስጥ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች የነዋሪውን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸውም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም