የአሁኑንና ቀጣዩን ትውልድ የሚያስተሳስሩ የልማት ስራዎችን በመገንባት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምእራፍ ለማሸጋገር የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

102

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 25/2015 የአሁኑንና ቀጣዩን ትውልድ የሚያስተሳስሩ የልማት ስራዎችን በመገንባት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምእራፍ ለማሸጋገር የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአዲስ አበባ የተገነባውን አንድነት የመኪና ማቆሚያ መርቀው ከፍተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ለውጡን ተከትሎ ትንናት ዛሬ እና ነገን የሚያስተሳስሩ የልማት ስራዎች እውን ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በዚህ ረገድ በአዲስ አበባ እውን የሆኑ የልማት ስራዎችን አንስተዋል።

የልማት ስራዎቹ የአሁኑን ብቻ ሳይሆን የሚመጣውን ትውልድ ታሳቢ ባደረገ መልኩ መገንባታቸውን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን የምናደረገው በልማት ስራ ብቻ ሳይሆን ሌብነትን በመታገል ጭምር መሆኑንም ገልጸዋል።

ሌብነት የኢትዮጵያ የልማት ጠንቅ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሊታገለው ይገባል ሲሉ አፅኖት ሰጥተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመረቀው አንድነት የመኪና ማቆሚያ 105 ሜትር ርዝመት፣ ስምንት ሜትር ስፋት እና 5 ሜትር ጥልቀት ያለው ሲሆን ወደ አንድነት ፓርክ መግቢያና መውጪያ የሚሆን ውብና ዘመናዊ መተላለፊያ አለው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም