ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉበት የ8 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በጅንካ እየተካሄደ ነው

150

ጂንካ (ኢዜአ) ህዳር 25/2015 በደቡብ ኦሞ በጅንካ ከተማ የ8 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው።

ውድድሩ “ለሰላምና አንድነት እሮጣለሁ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።

የጎዳና ላይ ሩጫው ዓላማ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በማጠናከር በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየተደረገ ያለውን ጥረት መደገፍ እንደሆነም ተመላክቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ በሚኒስቴሩ የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፈን ቸርነት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ፎዚያ እንዲሪስ ተገኝተው ውድድሩን አስጀምረዋል።

በውድድሩ ላይ አትሌት ኮማንደር ጌጤ ዋሚ፣ አትሌት ኮማንደር ቁጥሬ ዱለቻ፣ አትሌት ፋንቱ ሚጌሶን ጨምሮ ሌሎችም ታዋቂ አትሌቶች ታድመዋል።

መነሻውን ጂንካ መስቀል አደባባይ አድረጎ የተጀመረው የሩጫ ውድድር ጂንካ ሁለገብ ስታድዬም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም