የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በጅንካ ከተማ ነገ ይካሄዳል

274

ጅንካ (ኢዜአ) ሕዳር 24/2015 በደቡብ ኦሞ በጅንካ ከተማ የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ነገ ይካሄዳል።

ሩጫው "ለሰላምና አንድነት እሮጣለሁ" በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚካሄድ የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገልጿል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ፣ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፤የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ፎዚያ እንዲሪስ፣አትሌት ኮማንደር ጌጤ ዋሚ፣ አትሌት ኮማንደር ቁጥሬ ዱለቻንና አትሌት ፋንቱ ሚጌሶን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ አትሌቶች በውድድሩ ላይ ለመታደም ጅንካ መግባታቸው ተገልጿል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዳግም መኮንን እንዳሉት የሩጫው ዓላማ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በማጠናከር በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየተደረገ ላለው ሁሉን አቀፍ ጥረት ስኬት አበርክቶ የማድረግ አላማ ያለው ነው።

የሩጫው ውድድር ነገ ከማለዳው 12 ሰአት እንደሚካሄድና በርካታ አትሌቶችና የስፖርት አፍቃሪያን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም