የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ዜጎች አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበትና ባህሎቻቸውን የሚያስተዋውቁበት ኩነት ነው--አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር

99

አዲስ አበባ ሕዳር 24 ቀን 2015(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ዜጎች አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበትና ባህሎቻቸውን የሚያስተዋውቁበት ሁነት እየሆነ መጥቷል ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ።

May be an image of 3 people, people standing and indoor

17ኛው የኢትዮጵያ የብሄር፣ ብሔረሠቦችና ህዝቦች ቀን ከተማ አቀፍ የማጠቃለያ የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

የፓናል ውይይቱ እየተካሔደ ያለው "ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላም" በሚል ሃሳብ ነው።

በፓናል ውይይቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገርና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ቡዜና አልቃድርን ጨምሮ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ የህብረተሰብ አካላትና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል።

May be an image of 3 people, people standing, people sitting and military uniform

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን ህዝቦች አንድነታቸውን በማጠናከር ባህሎቻቸውን ልምዶቻቸውን የሚለዋወጡበት ነው።

በዓሉ ባለፉት አመታት አተገባበር ላይ በተለይ የተዛቡ ትርክቶች በማስተላለፍ ውስንነቶች እንደነበሩበትም አንስተዋል።

ከለውጡ በኋላ ይህን የተዛባ ትርክት ለማረም ተሞክሮ በርካታ አወንታዊ ለውጦች ተመዝግበውበታል ያሉት አፈ ጉባኤው "በዓሉ የአንዱ የማንነት መገለጫ የሌላው ማጌጫ እየሆነ መጥቷል" ብለዋል።

17ኛው የብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓልን ስናከብር ወንድማማችነትን ይበልጥ የምናጠናክርበት ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት።

May be an image of one or more people, people standing and indoor

ከተማ አቀፍ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ከህዳር ወር መጀመሪያ ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች በፓናል ውይይት ሲከበር ቆይቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም