በአዳማ ከተማ ግምቱ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ሲያጓጉዝ የነበረ ግለሰብ ተያዘ

197

አዳማ (ኢዜአ ) ህዳር 24/2015 በአዳማ ከተማ ግምቱ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን መያዙን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ ።

የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ ምክትል ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለኢዜአ እንደገለፁት በነዳጅ ጫኝ ተሳቢ ቦቴ ውስጥ ተጭኖ ከሶማሌ ጂግጂጋ ከተማ ወደ አዳማ በመጓጓዝ ላይ እያለ መያዙን ገልጸዋል ።

ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 68599 ኢ.ት የነዳጅ ጫኝ ቦቴ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ጭኖ በመጓዝ ላይ እያለ በአዳማ ከተማ መግቢያ ኩርፋ ኬላ ላይ መያዙን ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ተናግረዋል ።

ልባሽ ጨርቆችና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በነዳጅ ቦቴ ውሰጥ በመጫንና ነዳጅ አስመስሎ ኬላውን ለማለፍ ሲሞክር በፀጥታ ሃይሎች በትናንትናው ምሽቱ 12:30 ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን አመልክተዋል ።

አሽከርካሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልጸዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም