ዲፕሎማቶች በደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪዎችን እየጎበኙ ነው

97

ደብረ ብርሃን (ኢዜአ) ህዳር 23/2015 በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ዲፕሎማቶች የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ ሌሎች ኢንዱስትሪዎችን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝቱ እየተሳተፉ የሚገኙት 70 የሚሆኑ ዲፕሎማቶች ናቸው።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ዮሃንሰ አማረ በአማራ ክልል 3 ሺህ 412 አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ገለጻ አድርገውላቸዋል።

የክልሉ መንግስት በዚህ ዓመት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እንቅስቃሴ ለማሳለጥ ለሚያግዙ መሰረተ ልማቶች ግንባታ ከ450 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መድቦ  እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የዲፕሎማቶቹ ጉብኝት በክልሉ የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንቅስቃሴን ለማበረታታት የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል።

ዲፕሎማቶቹ ሰሞኑን በጎንደርና አካባቢው የሚገኙ የጎርጎራ ገበታ ለሃገር ፕሮጀክት፣ የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክና የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስታትን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም