17 ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሶማሌ ክልል ደረጃ በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
17 ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሶማሌ ክልል ደረጃ በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ ይገኛል
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 22/2015 17ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሶማሌ ክልል ደረጃ በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
ቀኑ "ህብረ-ብህራዊ እንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ስለመሆኑም ተጠቅሷል።
በስነ-ስርዓቱ ሀገራዊ ውይይትና ምክክር ለዘላቂ ሰላም ለህግ በላይነት መከበር ለሰላማችን መደላደል ነው በሚል የፓናል ውይይት እንደሚካሄድም ተገልጿል።
በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ላይ የሶማሌ ህዝብ በፌዴራሊዝም ስርአቱና ህገ-መንግስቱ የተረጋገጡለትን ዲሞክራሲያዊና ሠብዓዊ መብቶች ምንንነቶች የሚንፀባረቅበት የኪነ-ጥበብ ስራዎች በክልሉ ፓሊስ ባንድ እየቀረበ መሆኑም ተመላክቷል።
በዝግጅቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስተፌ ሙሁመድ፣ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አያን አብዲ፣ የብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ፣ የክልሉ ሀገር ሽማግሌዎች ሸንጎ አስተባባሪ ገራድ ኩልሚዬ ገራድ መሀመድ፣ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች መታደማቸው ተገልጿል።