የዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት ዋና ፀሃፊ ዶሪን ቦግዳን ማርቲን አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 20 ቀን 2015 የዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት ዋና ፀሃፊ ዶሪን ቦግዳን ማርቲን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዋና ፀሃፊዋ ኢትዮጵያ በምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ መምጣታቸው ተመላክቷል።

ዋና ጸሃፊዋ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ፒ ኤች ዲ) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዓለም ዓቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

በተመሳሳይ የናሚቢያ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢማ ቴዎፍሎስ ጉባኤውን ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም