በአፍሪካ የልሕቀት ማዕከል ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ዲፕሎማቶች በጎንደርና አካባቢዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን እየጎበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአፍሪካ የልሕቀት ማዕከል ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ዲፕሎማቶች በጎንደርና አካባቢዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን እየጎበኙ ነው
ጎንደር (ኢዜአ) ህዳር 20 ቀን 2015 ባለፉት ሳምንታት በአፍሪካ የልሕቀት ማዕከል የዲፕሎማሲ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶች በጎንደርና አካባቢዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን እየጎበኙ ነው።
ዲፕሎማቶቹ ዛሬ ማለዳ ጎንደር ከተማ ሲገቡ በአጼ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ በከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይና ሌሎች የከተማው አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዲፕሎማቶቹ በተመደቡባቸው ሀገራት የሚገኙ ቱሪስቶች ጎንደር ከተማና አካባቢውን መጥተው እንዲጎበኙ የቱሪዝም አምባሳደር በመሆን አካባቢውን በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
የዲፕሎማት አባላቱ በቆይታቸው በአለም ቅርስነት የተመዘገበውን የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስትን ጨምሮ የጎርጎራ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክትና ሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዲፕሎማቶቹ በአሁኑ ሰዓት የጎርጎራ ገበታ ለሃገር ፕሮጀክት ለመጎብኘት ወደ ስፍራው የተጓዙ ሲሆን ከሰዓት በኋላም የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስት እንደሚጎበኙ ታውቋል።
በጉብኝቱ ላይ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ተመድበው የሚሰሩ 70 የሚሆኑ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል።