የኢጋድ 48ኛው መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በካርቱም ይካሄዳል

22

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 19 /2015 የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት( የኢጋድ) 48ኛው መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ህዳር 21 ቀን 2015 በሱዳን ርዕሰ መዲና ካርቱም ይካሄዳል።

በስብሰባው ላይ በወቅታዊው የቀጠናው ሰላም እና ፀጥታ ፣በግጭት እና በተፈጥሮ የደረሱ አደጋዎች ፤ሰብአዊ እርዳታ ፣የምግብ ዋስትናና በሌሎች ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች በአጀንዳነት ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢጋድ ተቋማዊ ማሻሻያዎች የደረሰበት ሁኔታም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል።

ኢትዮጵያ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንደምትወከልም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም