በሶማሌ ክልል ከወተት፣ ከዶሮና ከንብ እርባታ ተገቢው ጥቅም እንዲገኝ ይሰራል

69

ጅግጅጋ (ኢዜአ) ህዳር 17 ቀን 2015  በሶማሌ ክልል በሚቀጥሉት አመታት ከወተት፣ ከዶሮና ከንብ እርባታ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳደሩ ይህንን የገሉጹት ዛሬ በክልል ደረጃ የተጀመረው እና ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም የሚተገበረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ባስጀመሩበት ወቅት ነው።

በክልሉ ለሚቀጥሉት ዓመታት የአርብቶ አደሩ ዋነኛ ሀብት የሆነውን የቤት እንስሳት ምርታማነት የሚያሳድጉ ስራዎች በትኩረት በመስራት አርብቶ አደሩ ህብረተሰብ ከእንስሳቱ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኝ ታቅዷል ነው ያሉት።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው የ"ሌማት ትሩፋት"በአራት ዓመታት ውስጥ በመተግበር የወተት፣ የዶሮና የማር ምርትን ከማሳደግ ጎን ለጎን ከአንድ ዓመት በፊት በክልሉ የተጀመረው የስንዴና የሰብል ልማት ስራ ጋር በጋራ የሚካሄዱ ይሆናል" ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም