አፍሪካ ለኢንዱስትሪ ልማት መረጋገጥ ትኩረት ልትሰጥ ይገባል-አቶ ደመቀ መኮንን

100

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 16 ቀን 2015 አፍሪካ በአህጉሩ የኢንዱስትሪ ልማት እንዲስፋፋና የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲጨምር በትኩረት መስራት እንደሚገባት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ኒጀር ርዕሰ መዲና ኒያሚ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት 17ኛ ልዩ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳስታወቁት አፍርካውያን ለኢንዱስትሪ ልማት ቅድሚያ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል።

የኢንዱስትሪ ልማት አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቷን ተጠቅማ እንድትለማና በአገሮች መካከል የሚካሄድ ንግድ እንዲስፋፋ አስፈላጊ መሆኑንም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ በማድረጉ ስኬታማ መሆኑን አቶ ደመቀ ጠቅሰው 22 የኢንዱስትሪና የተቀናጀ የግብርና የአንዱስትሪ ፓርኮች መገንባቱን አስታውቀዋል።

መንግስት አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ማድረጉንና መዋቅራዊ መሰናክሎችን በመፍታት ለግል ባለሃብቶች የተመቻቸ የስራ ሁኔታ ለመፍጠር እየሰራ ስለሰመሆኑ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም