ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የነጭ ሪባን ቀን ላይ ለመታደም ሐዋሳ ከተማ ገቡ

114

ሀዋሳ (ኢዜአ) ህዳር 16 ቀን 2015 ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በዓለም ለ31ኛ እና በኢትዮጵያ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው የነጭ ሪባን ቀን ላይ ለመታደም ሐዋሳ ከተማ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቷ ሐዋሳ ከተማ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተጨማሪም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ እና ሌሎች የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዓለም አቀፉ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን (የነጭ ሪባን ቀን) በዓለም ለ31ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ በሐዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም