ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ ኢዜአን እንደገና ለማቋቋም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሕዳር 15/2015 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ።

የምክር ቤቱ የሕግ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ተወያይቶበታል።

በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 1279/2015 የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ በአራት ድምጸ ተዓቅቦና በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን እንደገና ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የማቋቋሚያ አዋጁን አጽድቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም