ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠናና የተልዕኮ አቅጣጫ ሰጡ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠናና የተልዕኮ አቅጣጫ ሰጡ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 14 ቀን 2015 በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ የአመራር ልሕቀት አካዳሚ በመገኘት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠናና የተልዕኮ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ስልጠናው የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ተግዳሮቶች፣ ተስፋዎች፣ ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም ከዲፕሎማቶች በሚጠበቁ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል።
በስልጠናው ላይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተውጣጡ ወጣትና አንጋፋ ዲፕሎማቶች እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች መሳተፋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።