የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 14 ቀን 2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።
አየር መንገዱ ድጋፉን ያበረከተው ኤርባስ ከተባለ አውሮኘላን አምራች ጅርጅት እና አቪዬሽን ሳንስ ፍሮንተርስ ከተባለ የፈረንሳይ ኩባንያ ጋር በመተባበር መሆኑም አስታውቋል።
ከተደረጉት የድጋፍ አይነቶች መካከል ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ አልጋዎች፤ ወንበሮች፣ የተለያዮ አልሚ ምግቦች፣ ድንኳኖች እንደሆኑ ተገልጿል።
ድጋፉ የሚውለው ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል ነው ተብሏል።
ድጋፉንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስረክበዋል።