ዩኒቨርሲቲው በየኮሌጆቹ የተሻለ የምርምር ስራ ለሰሩ ተመራማሪዎች፣ ተማሪዎችና አሳታሚዎች እውቅና ሰጠ

147

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 12 ቀን 2015 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በየኮሌጆቹ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተመራማሪዎች፣ ተማሪዎችና አሳታሚዎች እውቅና ሰጥቷል።

በስድስት ኪሎ ካምፓስ በተዘጋጀው መርሃ-ግብር ላይ የዓመቱ ምርጥ ተመራማሪ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም አሳታሚዎች እውቅና ተሰጥቷል።

በእውቅና መርሀ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በተለያዩ የትምህርት መስኮች የምርምር ስራዎችን ያበረከቱ ምሁራን ተገኝተዋል።

በቅርቡ ከዩኒቨርሲቲው የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጣቸው ተመራማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ሽልማቱ የተሰጣቸው ምሁራን የምርምር ስራዎቻቸው አግባብ ባላቸው ጆርናሎች ያሳተሙ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ እና በማህበረሰብ ግልጋሎት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ መሆናቸውም ተገልጿል።

ዩንቨርሲቲው ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከ 2 ሺህ 800 በላይ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ የምርምር ስራዎች ለህትመት እንዳበቃ በመርሀ-ግብሩ ላይ ተገልጿል።

በምርምር ስራዎቹ ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መምህራን፣ ተማሪዎች እና አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል።

የዩንቨርሲቲው ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ባለፉት ስድስት ወራት 14 የምርምር ጽሁፎችን በማሳተም እውቅና ተበርክቶላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም