የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ለኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የራሱን አሻራ እያበረከተ ነው

274

ሰመራ (ኢዜአ) ህዳር 10/2015 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የራሱ አሻራ እያበረከተ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ገለፀች።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሰመራ ከተማ እያካሄደ ነው ።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ ምክትል ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፋዊ ውድድሮች እያስመዘገበች ያለው ውጤት አበረታች መሆኑንና እንደ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የበኩሉን እያደረገ ነው ።

ሀገርን ወክለው በሚደረጉ ውድድሮችም ኢትዮጵያን ያኮራ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ተንግራለች።

ባለፈው ዓመት በነበሩት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናና ሌሎች የወጣቶች ውድድሮች የተመዘገበው ውጤት ለአብነት በመጥቀስ።

"ለውጤታማነቱ ትልቁ ሚስጥር የእኔ ሳይሆን የእኛ በሚል በህብረት መስራት በመቻሉ ነው" ብላለች ።

በቀጣይም አትሌቲክሱን የበለጠ ለማሳደግ ለስፖርት መሰረት ልማት ግንባታ ትኩረት መስጠት እንደሚሻ ነው የገለጸችው።

በዚህ ጉባኤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የአባልነት ጥያቄ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ።

በእድሜ ተገቢነትና ተያያዥ ጉዳዮች ውይይት ማድረግ፣ የተሻሻለው የፌደሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮች የውይይት አጀንዳዎች ናቸው ።

እንዲሁም የ2014 ዓም የስራና ፋይናንስ የስራ አፈጻጸም ተወያይቶ ማጽደቅን ጨምሮ ፌደሬሽኑ ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የማበረታቻ ሽልማት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባኤው የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትን ጨምሮ የፌደሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ አባላትና የክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም