የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እያካሄደ ነው

25

ሕዳር 10 ቀን 2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እያካሄደ ነው።

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ የፌደሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትና የክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በጉባኤው የተሻሻለው የፌደሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ፣ የ2014 ዓ.ም የስራና የፋይናንስ አፈጻጸም እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የአባልነት ጥያቄ ላይ ውይይት ተደርጎ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ከአትሌቶች የእድሜ ተገቢነትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያም ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

ለአንድ ቀን በሚቆየው ጉባኤ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚያበረከት ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም