የስታትስቲክስ መረጃ በአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገትና ስራዎችን ለማሳለጥ ወሳኝ ድርሻ አለው…ዶክተር ፍጹም አሰፋ

147

አዲስ አበባ ሕዳር 9 2015 (ኢዜአ) የስታትስቲክስ መረጃ በአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ስራዎችን ለማሳለጥ ወሳኝ ድርሻ አለው ሲሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ።

የአፍሪካ ስታትስቲክስ ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው፡፡

No photo description available.

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ሚኒስትሯ እንዳሉት የስታትስቲክስ መረጃ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ስራዎችን ለማሳለጥ ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል።

በተለይም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያለው ሚና ወሳኝ እንደሆነ የገለጹት ዶክተር ፍጹም በዚህ ረገድ የስታትስቲክስ መረጃ መዘመን ላይ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ግብርና ትልቁ የኢኮኖሚ ምንጭና የስራ ዕድል የሚፈጠርበት መሆኑን አንስተው የተጠናከረ የስታትስቲክስ መረጃ ማቅረብ ለስራው መቃናት አጋዥ እንደሆነም ተናግረዋል።

ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መረጃን በጥራት መሰብሰብ እንደሚገባም ሚኒስትሯ አሳስበዋል።

የአፍሪካ ስታትስቲክስ ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ መከበር የጀመረው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት 1959 ዓ.ም እንስቶ እንደሆነ ተነግሯል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የስታትስቲክስ ቀን መታሰብ ዓላማ የስታትስቲክስ መረጃን ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ያለውን ፋይዳ ማስገንዘብ እንደሆነ ተገልጿል።

በመርሐግብሩ ላይ ሚኒስትሯን ጨምሮ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በከር ሻሌ እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም