ቀጥታ፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 22ኛ ዓመቱን አስመልክቶ ባዘጋጀው የእውቅና መርሐግብር ለአትሌቶችና ሌሎች ባለድርሻዎች እውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሕዳር 9/ 2015 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 22ኛ ዓመቱን አስመልክቶ ባዘጋጀው የእውቅና መርሐግብር ለአትሌቶችና ሌሎች ባለድርሻዎች እውቅና ሰጠ።

መርሐግብሩ ትናንት ማምሻውን "ኢትዮጵያዊነቴ ያኮራኛል" በሚል መሪ ሀሳብ ተከናውኗል።

May be an image of 3 people, people standing and indoor

በዚሁ መሰረት በወንዶች አትሌት ፀጋዬ ከበደ፣ ኮማንደር አትሌት ሞስነት ገረመው እና አትሌት ታምራት ቶላ ፤በሴቶች ውዴ አያሌው፣ አሰለፈች መርጊያ እና ያለምዘርፍ የኋላው የእውቅና ሽልማት የተሰጣቸው አትሌቶች ናቸው።

አትሌቶቹ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ለስኬታቸው መነሻ እንደሆናቸውና ከአትሌቲክሱ ማህበረሰብ ጋር እንዲተዋወቁ እድል ፈጥሮልናል ብለዋል።

ከአትሌቶቹ በተጨማሪ የቱሪዝም ሚኒስትር፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ በታላቁ ሩጫ ኢትዮጵያ የእውቅና ሽልማት ያገኙ ተቋማት ናቸው።

May be an image of 3 people and people standing

በእውቅና መርሐግብሩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ታዋቂ አትሌቶች፣የመገናኛ ብዙሃን አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የተጀመረው በ1994 ዓ.ም በአትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ አማካኝነት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም