ሀገራዊ የስታቲስቲክስ አቅምን ለመገንባት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው- የፕላንና ልማት ሚኒስቴር

24

አዲስ አበባ (ኢዜአ)ህዳር 8/2015 ሀገራዊ የስታቲስቲክስ አቅምን ለመገንባት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ነመራ ገበየሁ ተናገሩ።

 ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ያሉት የአፍሪካ የስታቲስቲክስ  ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ባለበት ሁነት ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በከር ሻሌን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ነመራ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ሀገራዊ የስታቲስቲክስ  አቅምን ለመገንባት  የተለያዩ ስራዎች  እየተሰሩ ነው።

ለዚህም ባለፉት አራት ዓመታት ተቋሙን ሪፎርም ለማድረግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

በቴክኖሎጂ የተደገፈና በአግባቡ የተደራጀ የስታቲስቲክስ  መረጃ ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የስታቲስቲክስ  መረጃ ለፖሊሲ ማውጫ፣ እና ለአገር ልማት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጠቁመው ጥራት ያለው ወቅታዊ መረጃ በአገር ደረጃም ሆነ በግለሰብ ደረጃ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም