ሚኒስትሮች እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን እየገበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ሚኒስትሮች እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን እየገበኙ ነው
ኮምቦልቻ (ኢዜአ) ህዳር 7 ቀን 2015 ሚኒስትሮች እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን እየገበኙ ነው።
በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ እየተሳተፉ ነው።
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ መኮንን ለኢዜአ እንደገለጹት፣ እንግዶቹ የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን የሥራ እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ነው።
በአሁኑ ወቅትም የኢንዱስትሪ ፓርኩ አንድ አካል የሆነው ''ካርቢኮ ኢትዮጵያ" የተሰኘ የጣሊያን ኩባንያ የማስፋፊያ ሥራዎች በመጎብኘት ላይ ናቸው።
በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ እየተመረቱ ያሉ የወንዶች ሙሉ ሱፍ፣ የሴቶች የእጅ ቦርሳ፣ ካልሲና ሌሎች የስፖርት አልባሳት ለውጭ ገበያ እየቀረቡ የውጭ ምንዛሬ እያስገኙ መሆኑን በዚሁ ጊዜ ተመላክቷል።
እንግዶቹ ኢንዱስትሪ ፓርኩን ለመጎብኘት ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።