የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ብሔራዊ ቡድን ወደ ታንዛኒያ አመራ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ብሔራዊ ቡድን ወደ ታንዛኒያ አመራ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሕዳር 6/2015 በአፍሪካ ዞን 3 የምስራቅ አፍሪካ የውሃ ዋና ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ብሔራዊ ቡድን ወደ ታንዛኒያ አመራ።
ሻምፒዮናው ከነገ ጀምሮ ለአራት ቀናት ይቆያል።
በሻምፒዮናው ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ዋናተኞች ዛሬ ወደ ታንዛኒያ ዳሬሰላም አቅንተዋል።
በውድድሩ ኢትዮጵያ በሁለት ታዳጊ ዋናተኞች የምትወከል ሲሆን፤ ታዳጊዎቹ በ17 ዓመትና በ14 ዓመት የእድሜ ክልል የሚወዳደሩ ናቸው።
ታዳጊዎቹ የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ባሳለፈው ነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም ቢሾፍቱ ባዘጋጀው የታዳጊዎች ውድድር ላይ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ስፖርተኞች መሆናቸው ተገልጿል።