የባንግላዴሽ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች መዋዕለ ነዋያቸውን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
የባንግላዴሽ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች መዋዕለ ነዋያቸውን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሕዳር 5 ቀን 2015 የባንግላዴሽ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የፀሐይ ኃይል ማመንጫን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች መዋዕለ ነዋያቸውን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር ናዝሩል ኢስላም እና ከባንግላዴሽ ባለሀብቶች ጋር መወያየታቸውን ኮሚሽኑ አመልክቷል።
ባለሀብቶቹ በኢትዮጵያ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ፣ በሞባይል ባንኪንግና በኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ባለሀብቶቹ ፍላጎት ባሳዩባቸው መስኮች የቀረጿቸውን ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
አምባሳደር ናዝሩል የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለባንግላዴሽ ባለሀብቶች በማስተዋወቅ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ ነው የገለጹት።