ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢምፔርያል ተሻጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ጎበኙ

93

ህዳር 4/2015 የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስተዳደሩ በተለያዩ አካባቢዎች በ2 ነጥበ 78 ቢሊዮን ብር እየገነባቸው ካሉ 6 ዘመናዊ የመሸጋገርያ ድልድዮች መካከል አንዱ የሆነውን የኢምፔርያል ተሻጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል።

ፕሮጀክቱ በአካባቢው ቀድሞ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በማስቀረት የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥና ለከተማዋም ዕድገት የራሱ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል።

May be an image of bridge

ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ገልጸው፣ “አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስና አበባ የማድረግ ጉዟችን በሁሉም መስክ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ማለታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም