የሰላም ስምምነቱ በታቀደለት መንገድ እንዲፈጸም መንግሥት እየሠራ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሰላም ስምምነቱ በታቀደለት መንገድ እንዲፈጸም መንግሥት እየሠራ ነው
በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በተታቀደለት መንገድ እንዲሄድ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት እየሠራ ነው።
በዚህም መሠረት በመከላከያ ሥር ወዳለው አብዛኛው የትግራይ አካባቢ ርዳታ እንዲደርስ እየተደረገ ነው። ወደ ተለቀቁት አካባቢዎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ቀስ በቀስ እየተጀመሩ ነው።
በሌሎች አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር እንዲቻል በታጣቂዎች የወደሙ መሠረተ ልማቶችን ለመጠገን ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።
ከዚሁ ጎን ለጎን በሰላም ስምምነቱ መሠረት የሕወሐት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት ዝርዝር ዕቅድ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አዛዥና የሕወሐት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢ መክረዋል።
በሰላም ስምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበትንና መከላከያ ወደ መቀሌ የሚገባበትን ዕቅድ ላይም ተስማምተዋል።
ዕቅዱም በቀጣይ ተግባራዊ ይደረጋል። ለዕቅዱ ተግባራዊነት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በስምምነቱ መሠረት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መንግሥት ያሳስባል።
ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ምአዲስ አበባ