የአፍሪካ ጋዜጠኞች የአህጉራቸውን ትክክለኛ ገጽታ ለዓለም ማሳየት ይኖርባቸዋል - አምባሳደር ሽብሩ ማሞ - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ጋዜጠኞች የአህጉራቸውን ትክክለኛ ገጽታ ለዓለም ማሳየት ይኖርባቸዋል - አምባሳደር ሽብሩ ማሞ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሕዳር 3/2015 “የአፍሪካ ጋዜጠኞች በስራቸው የአህጉራቸውን ትክክለኛ ገጽታ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል” ሲሉ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ገለጹ።
በታንዛንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ “አፍሪካ በፍጥነት እየተለወጠ ባለው የዓለም መገናኛ ብዙሃን ምህዳር ስትቃኝ” በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጀው የበይነ መረብ ውይይት ተካሄዷል።
አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ውይይቱ ጊዜውን የጠበቀ፣ ወሳኝ እና አስፈላጊ ነው ብለዋል።
“አፍሪካ ድንቅ ውበት ያላት ናትና የሰው ዘር መገኛ ናት፤ አፍሪካውያን የራሳችንን ታሪክ በራሳችን መናገር መጀመር ይኖርብናል” ብለዋል።
የአፍሪካ ጋዜጠኞች ያላችውን ክህሎትና እውቀት ለአፍሪካ ልማት በማዋል የአህጉሪቷን ትክክለኛ ገጽታ ለዓለም ማሳየት እንደሚኖርባቸው አመልክተዋል።
“የዓለም መገናኛ ብዙሃን ምህዳር በአፍሪካ ጉዳዮች ያለው ሚዛናዊነት የጎደለውና የተዛባ መረጃ ስርጭት” የተመለከቱ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የተለያዩ ሙያ ያላቸው የተለያዩ አገራት ተወካዮች እና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች በውይይቱ ላይ መሳታፋቸውም ገልጿል።