በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ዛሬ በዋሺንግተን ዲሲ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ዛሬ በዋሺንግተን ዲሲ ይካሄዳል
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 3 ቀን 2015 በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ዛሬ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ይካሄዳል።
ዝግጅቱ “ለሀገራዊ ጥሪ ወገናዊ ምላሽ” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚከናወን ኢዜአ ከሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ የዋሺንግተን ግብረ ኃይል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዝግጅቱ ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባል የገንዘብ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በከፈተው 1000439142786 ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ የሂሳብ ቁጥር እና በ’አይዞን ኢትዮጵያ’ የኦንላይን የገንዘብ ክፍያ አማራጭ ድጋፉን ማድረግ እንደሚችል አመልክቷል።
በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን በጦርነቱ ሳቢያ የሰብአዊ ድጋፍ ለሚያሻቸው ወገኖቻቸው ድጋፍ እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የመንግስት ተወካዮች፣አርቲስቶች፣ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ-ኢትዮጵያውያውንና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ የዋሺንግተን ግብረ ኃይል ከተለያዩ ተቋማትና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር እንዳዘጋጀው ተገልጿል።