የፕሪሚየር ሊጉ የሰባተኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘሙ

92

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሕዳር 3/2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘሙ።

ጨዋታዎቹ የተራዘሙት በድሬዳዋ አየር ንብረት ምክንያት የመጫወቻ ሜዳው ለማጫወት ምቹ ባለመሆኑ እንደሆነ የሊጉ አክሲዮን ማህበር ገልጿል።

አርባ ምንጭ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከ ፋሲል ከነማ፣ አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና ለገጣፎ ለገዳዲ ከ ወላይታ ድቻ የተራዘሙት ጨዋታዎች ናቸው።

ማህበሩ በድሬዳዋ በቀጣይ ቀናት የሚኖረውን የአየር ንብረት ሁኔታ ከተመለከተ በኋላ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ አመልክቷል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐግብር አራት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

ትናንት በተካሄዱ ጨዋታዎች ሐዋሳ ከተማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0፤ ኢትዮጵያ መድን ኢትዮ ኤሌትሪክን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

በዝናብ ምክንያት ሜዳው በመበላሸቱ ተጫዋቾች ኳስ ለማንከባበልና ለመቀባበል ሲቸገሩ ታይቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም