ቀጥታ፡

መከላከያ ሰራዊታችን ሁሌም ህዝባዊ ነው !

በፅኑ ህዝባዊ መሰረት ላይ የተገነባውና ከምንም በላይ ሃገሩንና ህዝቦቿን የሚያስቀድመው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት በትግራይ ክልል ከህዝቡ ጋር በመልሶ ግንባታና ልማት ስራዎች ላይ እየተሳተፈና እገዛ እያደረገ ይገኛል።

May be an image of 2 people and outdoors

ሰብል በደረሰባቸው አካባቢዎችም ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሰብል በመሰብሰብ የህዝብ ልጅነቱን ዳግም እያስመሰከረ ነው።

በደቡብ አፍሪካ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የነፈሰው የሰላም አየር የክልሉ ህዝብ ወደ መደበኛ ኑሮው እንዲመለስ በር ከፍቶለታል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከትግራይ ህዝብ ጋር በመሆን በግብርናና በሌሎች የመሰረተ ልማት መልሶ ግንባታ ስራዎችም በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም