የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአልባሳት ድጋፍ አደረገ

226

ሰቆጣ (ኢዜአ) ሕዳር 1 ቀን 2015 የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚኒስትሯ አማካሪ ሰለሞን አስፋው 16 ሺህ 124 የተለያዩ አልባሳትና ብርድ ልብሶች ድጋፍ ለዞኑ የሴቶች፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ካባ ሲሳይ አስረክበዋል።

ወይዘሪት ካባ ሚኒስቴሩ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደቀያቸው ተመልሰው እስኪቋቋሙ ድረስ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

አማካሪው አክለውም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱንና ይሄንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም