በክልሉ የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም አበረታች ነው- ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

142

ሐረር፤ ህዳር 1/2015 (ኢዜአ) ፡- በሐረሪ ክልል በካፒታል ፕሮጀክቶች እየተካሄዱ ያሉ ስራዎች አበረታች አፈጻጸም እንዳላቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዛሬ በተጀመረበት ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ አበረታች አፈጻጸም ካሏቸው መካከል  ከጀጎል ግንብ ጋር በተያያዘ ቅርስን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተከናወነ ያለው የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ ይገኝበታል።

በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ  የተዘመገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይ በክልሉ እየተገነባ የሚገኘው አው አባድር አለም አቀፍ ስታዲየምና የአርሶአደሮች ምርት መሸጫ ለአገልግሎት ለማብቃት ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበት አመልክተዋል።

በግምገማው መድረክ  የክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የስራ አፈጻጸም ላይ በመምከር  አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም