በፍትህ አካላት ላይ ተግባራዊ የተደረገው ሪፎርም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሻሻል እንዲመጣ አድርጓል-ኢንስቲትዩቱ

116

አዲስ አበባ ህዳር 1/2015/ኢዜአ/ መንግስት ጥናትን መሰረት በማድረግ በፍትህ አካላት ላይ ተግባራዊ ያደረገው ሪፎርም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሻሻል እንዲመጣ ማድረጉን የፌደራል የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፊ ቡላ ገለጹ፡፡

የፌደራል የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የፍትህና ሕግ ጥናትና ምርምር ውጤቶችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው፡፡

በዚህም የፍርድ ቤት ውሳኔዎችና የህዳጣን ማህበረሰብ መብቶችን አስመልክቶ የተሰሩ አምስት የጥናትና ምርምር ውጤቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ እንዳሉት፤ መድረኩ  የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ለትግበራ ለማቅረብ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት ማሰባሰብን ያለመ ነው፡፡

መንግስት በተለይም ከለውጡ በኋላ በፍትህ አካላት ላይ በጥናት ላይ ተመስርቶ ባደረገው ሪፎርም በፍትህ አካላት ላይ የሚስተዋለው ችግር መሻሻል እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን አገልግሎቱን ይበልጥ ለማሻሻል ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም ነው የጠቆሙት፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም