የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1ኛ ልዩ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1ኛ ልዩ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ ህዳር 1/2015/ኢዜአ/ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1ኛ ልዩ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በጉባኤው የሁሉም ክልሎች ተወካዮች እየተሳተፉ ሲሆን፤ የምክር ቤቱ 100 ቀን እቅድና ክንውን ሪፖርት ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም ረቂቅ የመተዳደሪያ ደምብ ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን፤ በምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አቅራቢነት የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ አባላት ሹመት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ማድረግም በጉባኤው ከተያዙ አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡