የፕሪሚየር ሊጉ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የፕሪሚየር ሊጉ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሕዳር 1/2015 በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።
የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልቂጤ ከተማ ከቀኑ 10 ሰአት፤ ድሬዳዋ ከተማ ከመቻል ከምሽቱ 1 ሰአት በድሬዳዋ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ነገ ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮ ኤሌትሪክ ከቀኑ 10 ሰአት እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከሐዋሳ ከተማ ከምሽቱ 1 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ-ግብር እስከ ሕዳር 4 ቀን 2015 ዓ.ም ይቆያል።
ከ6ኛ እስከ 10ኛ ሳምንት ያሉ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታዲየም እንደሚካሄዱ ይታወቃል።