በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መቀመጫቸውን በጅቡቲ ላደረጉ ዲፕሎማቶች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጠ

96

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥቅምት 30 ቀን 2015 በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መቀመጫቸውን በጅቡቲ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጠ።

ኤምባሲው በኢትዮጵያ መንግስትና በሕወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነትና ስምምነቱን ተፈጻሚ ለማድረግ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን አስመልክቶ ገለጻ ማድረጉን አመልክቷል።

በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋምና የመልሶ ግንባታ ስራዎች አሁን ያሉበት ደረጃ በማብራሪያው መዳሰሱን ጠቁሟል።

ኤምባሲው በአገሪቷ መቀመጫቸውን ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የሚሰጠው ማብራሪያ ነገም እንደሚቀጥል ገልጿል።

ባለፈው ሳምንት የሰላም ስምምነቱን አስመልክቶ መንግስት በኢትዮጵያ ለሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ገለጻ ማድረጉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም