የክቡር ዶክተር አሊ ቢራ ስርዓተ ቀብር በድሬዳዋ ለገሀሬ እስላም መቃብር ተፈጸመ - ኢዜአ አማርኛ
የክቡር ዶክተር አሊ ቢራ ስርዓተ ቀብር በድሬዳዋ ለገሀሬ እስላም መቃብር ተፈጸመ
ድሬዳዋ (ኢዜአ) ጥቅምት 29/2015 የክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ስርዓተ ቀብር በድሬዳዋ ለገሀሬ እስላም መቃብር ተፈጸመ ።
የአርቲስት አሊ ቢራ አስክሬን የሽኝት እና የጸሎት ፕሮግራም በድሬዳዋ ከተማ እስታዲየም የተካሄደ ሲሆን የቀብር ስነስርዓቱ ላይ ወዳጅ ዘመድ፣ሙያ አጋሮቹ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች ፣በርካታ የድሬዳዋ እና አካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል ።
ክብር ዶክተር አርቲስት ዓሊ ቢራ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በ75 ዓመቱ ከትናንት በስቲያ ሕይወቱ ማለፉ ይታወቃል።
አርቲስቱ ስለአንድነት ፣አብሮነት ፣ፍቅር ፣ሰላምና ፍትህን ጨምሮ በበርካታ ስራዎች ላይ አቀንቅኗል።