ስንዴን ወደ ውጭ መላክ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከባለሃብቶች ጋር ውይይት ተደረገ

137

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥቅምት 29 ቀን 2015 የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ስንዴን ወደ ውጭ መላክ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከስንዴ ላኪ ባለሃብቶች ጋር ውይይት አድርጓል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ ሀገራችን ኢትዮጵያ የእርዳታ ስንዴን ከማስገባት አልፋ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወደ ውጭ የሚላከው ስንዴ ከሀገር ውስጥ ፍጀታ የተረፈ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ ለዚሁም ይረዳ ዘንድ በመንግስት በኩል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ተሻለ በልሁ በበኩላቸው በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የጥራት ጉዳይ ለድርድር መቅረብ እንደሌለበትና ላኪዎችም ይህንን ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

ላኪዎች በበኩላቸው ሃገሪቱ ከዚህ በፊት የነበራት ገጽታ ተቀይሮ ከስንዴ አስመጪነት ወደ ላኪነት መሸጋገሯ የሃገሪቱን መልካም ገጽታ ለመገንባት መልካም አጋጣሚ በመሆኑ በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን እና የተጣለባቸውን ሃገራዊ ሃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም