ኢትዮጵያ በለንደን እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የጉዞና ቱሪዝም ዝግጅት ላይ እየተሳተፈች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በለንደን እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የጉዞና ቱሪዝም ዝግጅት ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥቅምት 28/2015 ኢትዮጵያ በለንደን እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የጉዞና የቱሪዝም ዝግጅት ላይ እየተሳተፈች ነው።
“ወርልድ ትራቭል ማርኬት ለንደን” የሚል ስያሜ ያለው ዝግጅት ዛሬ በለንደን ከተማ ተጀምሯል።

በሁነቱ መክፈቻ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ዳዊት፣በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀጠናዊ ስራ አስኪያጅ ሄኖክ ውብሸት ተገኝተዋል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ የጉዞና የቱሪዝም ስራዎች የሚተዋወቅበት ድንኳን(ፓቪሊዮን) በይፋ መከፈቱን በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
“ወርልድ ትራቭል ማርኬት ለንደን” እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ባለድርሻ አካላት የጉዞና የቱሪዝምና ዘርፍን ማሳደግና አዳዲስ አማራጮችን መፈለግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተገልጿል።