መንግሥት በታንዛኒያ በመንገደኞች አውሮፕላን በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
መንግሥት በታንዛኒያ በመንገደኞች አውሮፕላን በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገለጸ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥቅምት 28/2015 የኢትዮጵያ መንግሥት የታንዛኒያ የመንገደኞች አውሮፕላን በቪክቶሪያ ሐይቅ ላይ ተከስክሶ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ ለታንዛኒያ ሕዝብና መንግሥት ሃዘኑን ገልጿል።
በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጾ፤ ለሟች ለቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን በመመኘት በአደጋው የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በፍጥነት እንዲያገግሙም ተመኝቷል።