በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
ጥቅምት 27/ 2015 (ኢዜአ) በ2015 ዓ.ም በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ሃዋሳ ከተማ ከፋሲል ከነማ ከቀኑ 7 ሰአት እንዲሁም የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአርባ ምንጭ ከተማ ከቀኑ 10 ሰአት በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ትናንት በተደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ መቻልን 1 ለ 0፤ ወልቂጤ ከተማ ኢትዮ ኤሌትሪክን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።