ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በምእራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ በመገኘት የስንዴ ምርት አሰባሰብን ጎበኙ

ጥቅምት 26/2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በምእራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ በመገኘት የስንዴ ሰብል አጨዳና ምርት አሰባሰብ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ ጨምሮ ሌሎች የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

በዞኑ125 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም በስንዴ የለማ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም ዘመናዊ የግብርና ማሽኖችን በመጠቀም የምርት መሰብሰብ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም