የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ወጣቶች የደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር በጋራ እየሰሩ ነው

72
አዲስ አበባ መስከረም 15/2011 የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከበር ለማድረግ በየአካባቢያቸው ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገለጹ። በአዲስ አበባ የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የደመራን በዓል ከተለያዩ ቤተክርስትያናት ወደ መስቀል አደባባይ በመሄድ   ያከብራሉ። ነገ የሚከበረው ይህ በዓል በሠላማዊና ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከናወን ከአካባቢያቸው ወጣቶች ጋር በመሆን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ተማሪዎቹ ለኢዜአ ተናግረዋል። በመስቀል አደባባይና በየአብያተ ክርስትያናት በሚካሄደው ስነ-ስርዓት የጎላ ተሳትፎ ለማድረግና የበዓሉ ድምቀት ለመሆንም ተዘጋጅተዋል። ዲያቆን አዲሱ ጌታቸው ከቅድስት ስላሴ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች  ቀደም ብለን  ከወጣቶች ጋር በመመካከር ወጣቶችም የራሳቸውን ድርሻ በመወጣት፤  በዓሉ ሰላማዊ እንዲሆን እየሰራን ነው ብሏል፡፡ በዓሉ በሰላምና በፀጥታ እንዲከበር እንዲሁም ያሳለፍናቸው የሀዘን ሳምንታቶች እንዳይደገሙ  ከወዲሁ ቅድመ ጥንቃቄዎችን እያደረግን ነው ከሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ውጭ ካሉት ወጣቶች ጋር በመተባበር ያለው  ወጣት አቤል ፍቃዱ ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሄር አብ ዕጸ ጳጦስ ካቴድራል ሰንበት ተማሪ፡፡ የመስቀል ደመራ በዓለም የማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ ሲሆን በርካታ የውጭ አገር ዜጎች በዓሉን ለመታደም ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።                          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም