ቀጥታ፡

ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መሰረት የሚጥል ነው- ኢክናስ

ጥቅምት 25 ቀን 2015 (ኢዜአ) የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ(ኢክናስ) ከትናንት በስትያ በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው ስምምነት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና አንድነት መሰረት የሚጥል መሆኑን ገለጸ።

ስምምነቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በመንግስትና በሕወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በደስታ እንደሚቀበለው ገልጿል።

የሰላም ስምምነቱ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ፣የሰላም እና የአንድነት ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት መሰረት የሚጥል ነው በማለት ለስምምነቱ ተግባራዊነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርቧል።

በተለይ የዳያስፓራው ማህበረሰብ የወደሙ መሰረተ-ልማቶችን በመገንባት እና የሰብዓዊ እርዳታን በመለገስ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው በመግለጽ ዳያስፖራው ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አስገንዝቧል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን ለቆሙ የኢትዮጵያ ወዳጆችና አጋር አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም