በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን የግፍ ጭፍጨፋ የሚዘክርና የሰላም ስምምነቱን የሚደግፍ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው

77

ጥቅምት 24 2015(ኢዜአ) በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን የግፍ ጭፍጨፋ ሁለተኛ ዓመት የሚዘክርና በፌዴራል መንግስትና በሕወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው።

“በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ መቼም አንረሳውም”፣የተደረገውን ስምምነት እንደግፋለንና ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመከባበርና በፍቅር መኖር አለበት” የሚሉ መልዕክቶች በሰልፉ ላይ እየተላለፉ ይገኛሉ።

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንና የሰላም ስምምነቱ ስኬታማ እንዲሆን በቂ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባውም ሰልፈኞቹ በያዟቸው መልዕክቶች ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም