በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የተካሔደው የሰላም ውይይት በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ ያላችሁ--ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ

82

ጥቅምት 24 ቀን 2015 (ኢዜአ) የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በደቡብ አፍሪካ ፐሪቶሪያ በመንግስት እና በሕወሓት መካከል የተደረሰውን ስምምነት አደነቁ።

ፕሬዝዳንቱ በቲውተር ገጻቸው ባስቀመጡት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በፕሪቶሪያ የተካሄደው ስምምነት በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

“በስምምነቱ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ደህንነት፣ ሰላምና ብልጽግና እንዲመጣ ሁሉንም ጥረት በማድረጋችሁ እንኳን ደስ ያላቸሁ” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም