በኢትዮጵያ ለሚደረገው የሰላም ግንባታ ሂደት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን--የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

114

ጥቅምት 24 ቀን 2015 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ለሚደረገው የሰላም ግንባታ ሂደት ተርኪዬ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ተርኪዬ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት የተሰማትን ደስታ ገለጻ አድናቆት እንዳላትም አስታውቃለች።

የተደረሰው ስምምነት ዘላቂ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለንም ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡

የሰላም ውይይቱ እንዲካሄድ ጥረት ላደረጉ እና ላስተባበሩ አካላትም ምስጋና እናቀርባለን ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም